አማርኛ

ብፁዕ ነህ?

ኦክቶበር 8፣ 2022
በመደበኛው ዘመን የሃያ ሰባተኛው ሳምንት ቅዳሜ
የዛሬ ንባባት

ቪዲዮ

ኢየሱስ እየተናገረ ሳለ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ «የተሸከመህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው» አለችው። እርሱም፣ «ይልቅስ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙና የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው» ብሎ መለሰ።  ሉቃስ 11:27-28

የእግዚአብሔርን ቃል ትሰማለህ?  የምትሰማው ከሆነስ፣ ትጠብቀዋለህ?  እንዲህ ከሆነ፣ በጌታችን በእውነት ከተባረኩት መካከል እንደሆንህ ራስህን ልትቆጥር ትችላለህ።

ትኩረት የሚስበው፣ በዚህ ክፍል ኢየሱስን የምታነጋግረው ሴት፣ እናቱ እርሱን በመፀነሷና በማጥባቷ ብፅዕት እንደሆነች በመናገር እያከበረቻት መሆኑ ነው።  ኢየሱስ ግን በዚህ መልሱ እናቱን ከዚያ በላቀ ሁኔታ ያከብራታል።  ከማንም በላይ የእግዚአብሔርን ቃል ስለምትሰማና ፍጹም በሆነ ሁኔታ ስለምትጠብቀው፣ ያከብራታል፤ ብፅዕትም ይላታል።

መስማትና መፈጸም እጅግ የተለያዩ ሁለት ነገሮች ናቸው።  ሁለቱም በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቁርጠኝነት ይጠይቃሉ።  በመጀመሪያ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ማለት በጆሮ ድምፁን መስማት ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ብቻ አይደለም።  በዚህ አውድ «መስማት» ማለት እግዚአብሔር ለነፍሳችን ተናግሯል ማለት ነው።  ከአንድ አካል፣ ማለትም ከኢየሱስ ራሱ ጋር ግንኙነት እያደረግን፣ ለእኛ ሊያስተላልፈው የሚፈልገውን ሁሉ እንዲያስተላልፍልን እየፈቀድንለት ነው ማለት ነው።

ኢየሱስ ሲናገር መስማትና የሚናገረውን በልባችን ማስረጽ ፈታኝ ሊሆን ቢችልም፣ ከዚያ በኋላ የተናገረውን በሕይወታችን እስከምንኖር ድረስ ቃሉ እንዲለውጠን መፍቀድ ከዚያም የበለጠ ፈታኝ ነው።  ብዙ ጊዜ እጅግ መልካም ሐሳብ ሊኖረን ይችላል፤ ሆኖም የእግዚአብሔርን ቃል በመኖር ያንን ሐሳብ ወደ ተግባር ማድረስ ያቅተናል።

ዛሬ ስለ መስማትም ሆነ ስለ መጠበቅ አሰላስል።  በመስማት ጀምር፤ በየቀኑ ኢየሱስ ካንተ ጋር ግንኙነት እንዲያደርግ ትፈቅድለታለህ ወይስ አትፈቅድለትም ብለህ አሰላስል።  ከዚያም፣ እርሱ እንደተናገረው የምታውቀውን በሕይወትህ እየኖርከው እንደሆነ አሰላስል።  ለዚህ ሂደት ያለህን ቁርጠኝነት አድስ፤ አንተም በእውነት ብፁዕ እንደሆንህ ታያለህ!

ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቃል ሆይ፣ ስትናገረኝ ልስማህ። በነፍሴ ውስጥ ልገናኝህ፣ ቅዱስ ቃልህንም ልቀበል። ለእኔ ያዘጋጀሃቸውን በረከቶች እንዳገኝ፣ ያንን ቃል በሕይወቴ በተግባር ላውለው። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

አዲስ!


ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ ውስጣዊ ጉዞ፦
ከአቪላዋ ቅድስት ቴሬዛ የተወሰዱ ማሰላሰያዎች

ተጨማሪ የወንጌል ማሰላሰያዎች

በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ማሰላሰያዎች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት

የቅዳሴ ንባብ አማራጮች

ተለይቶ የቀረበ ምስል፦ በሕዝብ መካከል ጮኻ የምትናገር ሴት፣ በጄምስ ቲሶ፣ በዊኪሚዲያ ኮመንስ በኩል