አማርኛ

እውነተኛ ሀብት

ማርች 12፣ 2020
የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ሐሙስ
የዛሬ ንባቦች

ድሃው ሰው በሞተ ጊዜ፣ መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት።  ሀብታሙም ሞቶ ተቀበረ፤ በሲኦልም በሥቃይ ላይ ሳለ፣ ዓይኖቹን አንሥቶ አብርሃምን ከሩቅ፣ አልዓዛርንም ከጎኑ አየ።  ሉቃስ 16:22–23

መምረጥ ቢኖርብዎ፣ የትኛውን ይመርጣሉ?  ሀብታም ሆነው፣ ሐምራዊ ልብስ ለብሰው፣ በዚህ ዓለም ሊመኙት የሚችሉትን ሁሉ አግኝተው፣ በየቀኑ በቅንጦት መመገብን?  ወይስ በቁስል ተሸፍነው፣ በደጃፍ እየኖሩና በረሃብ እየተሠቃዩ ድሃ ለማኝ መሆንን?  በላይኛው ሲታይ መመለሱ ቀላል ጥያቄ ነው።  ሲጀመር ሲታሰብ፣ የሀብትና የምቾት ኑሮ ይበልጥ ማራኪ ነው።  ነገር ግን ጥያቄውን በላይኛው ብቻ ማየት የለብንም፤ በጥልቀት ተመልክተን፣ በእነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት በሙሉ እና የውስጥ ሕይወታቸው ለዘላለም በሚኖሩት ነፍሶቻቸው ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ማሰብ አለብን። 

ድሃው ሰው በሞተ ጊዜ፣ “መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት።”  ስለ ሀብታሙ ግን መጽሐፍ ቅዱስ “ሞቶ ተቀበረ”፣ ወደ “ሲኦልም ሄዶ በዚያ በሥቃይ ላይ ነበር” ይላል።  እንዴት ያሳምማል!  አሁን ማንን መምሰል ይመርጣሉ?

በዚህ ሕይወትም ሆነ በሚመጣው ሕይወት ሀብታም መሆን የሚመኝ ቢሆንም፣ የኢየሱስ ታሪክ ዋና መልእክት ይህ አይደለም።  የታሪኩ መልእክት ቀላል ነው፤ በዚህ ምድር ሳለን ንስሐ መግባት፣ ከኃጢአት መመለስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት መስማት፣ ማመን እና ዓይኖቻችንን በእውነተኛው ግባችን፣ በሰማይ ሀብት ላይ ማድረግ አለብን።

በዚህ ሕይወት ሀብታም ወይም ድሃ መሆንዎ በእውነቱ ዋናው ጉዳይ መሆን የለበትም።  በውስጣችን ወደዚህ ጽኑ እምነት መድረስ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ግባችን መሆን አለበት።  ትኩረታችን ሰማይና በዚያ የሚጠብቀን ሀብት መሆን አለበት።  ለሰማይም የምንዘጋጀው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና በታላቅ ልግስና ምላሽ በመስጠት ነው። 

ሀብታሙ ሰው በደጃፉ የተኛውን ድሃ ክብርና ዋጋ በማየት፣ በፍቅርና በምሕረት ወደ እርሱ በመቅረብ በዚህ ሕይወት ምላሽ መስጠት ይችል ነበር።  ነገር ግን ይህን አላደረገም።  በራሱ ላይ ከመጠን በላይ አተኩሮ ነበር።

ዛሬ፣ በእነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል ባለው እጅግ ግልጽ ልዩነት፣ በተለይም እያንዳንዳቸውን ይጠብቅ በነበረው የዘላለም ሕይወት ላይ ያሰላስሉ።  የዚህን ሀብታም ሰው ኃጢአተኛ ዝንባሌዎች አንዳንዶቹን በራስዎ ሕይወት ውስጥ ካዩ፣ ከእነዚህ ኃጢአቶች ንስሐ ይግቡ፤ ዛሬውኑ ንስሐ ይግቡ። የሚያገኙትን እያንዳንዱን ሰው ክብርና ዋጋ ይመልከቱ።  በራስ ወዳድነት ደስታና በቅጥ ያጣ ኑሮ ተውጠው፣ በራስዎ ላይ ይበልጥ የማተኮር ዝንባሌ ካለዎት፣ እውነተኛ የመንፈስ ድህነትን ለመቀበል ይፈልጉ። ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ለመጣበቅ፣ እርሱ የገለጠልንን ሁሉ ሙሉ በሙሉ በመቀበል የሚገኘውንም የበረከት ብዛት ለማግኘት ይትጉ።

ጌታ ሆይ፣ እባክህ ከራስ ወዳድነቴ ነፃ አውጣኝ።  በዚህ ፈንታ በሰዎች ሁሉ ክብር ላይ ትኩረቴን እንዳደርግና እነርሱን ለማገልገል ራሴን ሙሉ በሙሉ እንድሰጥ እርዳኝ።  በድሆች፣ በተሰበሩትና በትሑታን ውስጥ የአንተን ምስል ላግኝ።  በሕይወታቸውም ውስጥ ያንተን መገኘት ሳገኝ፣ የምሕረትህ መሣሪያ ለመሆን እየፈለግሁ፣ አንተን በእነርሱ ውስጥ ልውደድህ።  ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

በመስቀሉ ሥር 40 ቀናት – አሥራ አምስተኛ ማሰላሰል – የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና መጠበቅ

ለዐቢይ ጾም የሚረዱ ግብዓቶች

ተጨማሪ የወንጌል ማሰላሰያዎች

በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ማሰላሰያዎች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት

የቅዳሴ ንባብ አማራጮች